የፈጠራ ስራዎችን የሕዝብን ችግር ሊቀርፉ በሚያስችል መልኩ አድርጎ መስራት ይገባል።

2026-04-09

የፈጠራ ስራዎችን የሕዝብን ችግር ሊቀርፉ በሚያስችል መልኩ አድርጎ መስራት ይገባል።

የፈጠራ ስራዎችን የሕዝብን ችግር ሊቀርፉ በሚያስችል መልኩ አድርጎ መስራት ይገባል።

(መጋቢት 30/2018) በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና ሣይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤቶች በመተባበር የ2018 የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን እና ውድድር አከናውነዋል።

የተካሄደው የሳይንስና የሂሳብ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን እና ውድድር አስመልክቶ የማጠቃለያ የፓናል ውይይት ተካሄዷል።

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዶ አሊ የፈጠራ ስራዎችን ማዳበር፣ ቴክኖሎጂን የሕዝብ ችግርን ሊቀርፍ የሚችል አድርጎ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የፈጠራ ስራ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ከፍ በማድረግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራ ለመስራት በሚያስችል መልኩ መሰራት እንዳለበት አስረድተዋል።

በቀጣይ ማዕከላትን በማጠናከር ተቋማት በመቀናጀት የሚደረገው ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ የሚቀጥልና ለቀጠይ ውድድር ዝግጅት የሚደረግ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

የከተማው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኑረዲን መሃመድ በኤግዚቤሽኑ ተስፋ የሚሰጡ ስራዎች መቅረባቸውን ገልፀዋል።

በቀጣይም ከፍ ማድረግ እንደሚገባ እና ስራው በእውቀት ለመደገፍ እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

የፈጠራ ስራን የኢኮኖሚ ምንጭ አድርጎ መስራት ይገባል ያሉት አቶ ኑረዲን ተቋማት በቅንጅት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉም ጠቁመዋል።
Back to News